ስለ አድማጮህ መማር እና አድማጮችህ ከፕሮግራምህ የሚጠብቁትን ጉዳይ ማወቅ

ማስታወሻ ለ አዘጋጆች

አንድ የሬድዮ ጣቢያ ስለፕሮግራሞቹ እና አድማጮች ሊያደምጡት ስለሚፈልጉት ነገር ከአድማጮቹ ግብረመልስ የሚያገኝ ከሆነ የጣቢያው ፕሮግራሞች የአድማጮችን ፍላጎት የሟሟላት ዕድሉ ከፍ ያለ ይሆናል፡፡

ከአድማጮችህ ፍላጎት ጋር የሚጣጣም ስኬታማ የግብርና ሬድዮ ለመፍጠር፡

1) አድማጮችህን እወቅ
2) ለእነሱ አስፈላጊ የሆነው የግብርና መረጃ ምን እንደሆነ እወቅ
3) አርሶ አደሮች ለእነሱ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ሊወያዩ የሚችሉበትን ሁኔታ እወቅ

ጣቢያህ ለመጨረሻ ጊዜ የአድማጮችህ የግብርና ሁኔታን አስመልክቶ ጥናት ያካሄደው መቼ ነበር ? ምናልባት በድጋሚ የሚጠናበት ጊዜ ሊሆን ይችላል!

ክፍል 1:አርሶ አደር አድማጮች ምን ዓይነት መረጃ ይፈልጋሉ?

መግቢያ

አርሶ አደር አድማጮችህ ምን ዓይነት መረጃ ይፈልጋሉ የሚለውን ለማወቅ በጣም አስፈላጊ የመረጃ ምንጭህ ምንድነው? በእርግጥ አድማጭህ አርሶ አደሩ ነው!

የጥናት ዘዴዎቹ ምንም እንኳ በዚህ የመረጃ ማስታውሻ የተጠቀሱ ቢሆንም ማህበረሰቡ ድረስ በመሄድ መጎብኘት በእጅጉ ይመረጣል፡፡ በመንደሮች ውስጥ ስብሰባዎችን አመቻች፤ በትራነሰፖርት ሄደህ ከአርሶ አደር ቡድኖች ጋር ተገናኝ፡፡ ሴት አርሶ አደሮች በወንዶች ፊት ለማውራት የሚቸገሩ ከሆነ ከሴቶቹ ጋር ለብቻ ስብሰባ አመቻች፡፡

አንዳንድ ሬድዮ ጣቢያዎች ከአርሶ አደሮች ጋር ሲነጋገሩ፤ ድምጾቻቸውን ሲቀርጹ፤ እና አርሶአደሮች ስለሚፈልጉት መረጃ ለመነጋገር የሚያስችላቸው ውይይቶችን ሲያካሂዱ ረጅም ጊዜአቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ሌሎች ሬድዮ ጣቢያዎች ማሳዎች ድረስ ጉዞ ማድረግ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡ሆኖም በጣቢያህ ሁኔታው ምንም ቢያስቸግርም በተቻለ መጠን ከ አርሶ አደር አድማጭህ ጋር መገናኘቱ ቁልፉ ጉዳይ ነው፡፡

ምንጮችህን መሰረት በማድረግ ከአድማጭ ማህበረሰብህ ጋር ቀድሞ በነበረህ የግንኙነት መጠን እና በአድማጭ ጥናትና ስልጠና ባለህ የዕውቅና መጠን አድማጭ ማህበረሰብህን በምትጎበኝበት ጊዜ ልታካሂዳቸው የምትችላቸው በርካታ የጥናት ተግባራ አሉ፡፡ ሁሉም ጥናቶች ከአርሶ አደሮች ጋር መገናኘትን ያካትታሉ፡፡ ስለሆነም በጥሩ አሳታፊ ፕሮግራም ዋናው ግብአት ግንኙነት መገንባት መሆኑን አትዘንጋ፡፡

በአድማጭ ጥናት ላይ ጠቂት ምንጭ ወይም ስልጠና ያላቸው ጣቢያዎች ወይም ከማህበረሰባቸው ጋር ውሱን ግንኙነት ያላቸው ጣቢያዎች ቀጥሎ ከተዘረዘሩት አምስት የጥናት ስራዎች መካከል የተወሰኑትን መሞከር ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

ጠቢያህ ከሚያዳምጥህ ማህበረሰብ ጋር በአንጻራዊነት አነስተኛ ከነበረ ዛፍ ስር የሚደረጉ ዓይነቶች ኢመደበኛ በሆነ መልኩ ከአርሶ አደሮች ጋር መገናኘት ፤ በእነዚህ ኢመደበኛ ግንኙነቶች ጥቂት ሰፋፊ ጥያቄዎችን ማቅረብ እናም በጥያቄዎችህ ላይ በነጻነት በስፋት እንዲነጋገሩበት ማድረግ ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ ጣቢያህ እነሱን እንደ አርሶ አደሮች በተሸለ መልኩ እንዴት ማገልገል እንደሚችል መጠየቅ ትችላለህ፡፡በተጨማሪም ለግብርናቸው መሻሻል የሚያስፈልጋቸው ዋና መረጃ ምን እንደሆነ መጠየቅ ትችላለህ፡፡

እንዲህ ክፍት በሆነ አቀራረብ መጠቀም አርሶ አደሮች ይዘትን በመወሰን ወይም የሬድዮ አጀንዳህን በመለየት በነፃነት እንዲሳተፉ ይረዳቸዋል፡፡ በግብርና ጉዳዮች ግብረመልስ እየጠበቅክ ከሆነ ጥያቄዎችህን በተቻለ መጠን በሰፊው ግብርና ላይ አዘጋጃቸው፡፡ምናልባትም አኗኗራቸውንም ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ (የአርሶ አደሮች መተዳደሪያ ሁሉንም የአኗኗር ዘዴአቸውን ያጠቃልላል)

ከአድመጭ ማህበረሰቦቻቸው ጋር የተሻለ ምንጮች ፤ ስልጠና እና መደበኛ ግንኙነት ያለቸው ጣቢያዎች ቀጥሎ በዚህ የመረጃ ሰነድ የሚጠቀሱ ሶስቱን ተጨማሪ የምርምር ስራዎችን እንዲሞክሩ ይበረታታሉ፡፡ ሆኖም ከተጠቀሱት ውስጥ የትኛውንም መሞከር ትችላለህ፡፡

ቀጥሎ ከተጠቀሱት ተግባራት መካከል የተወሰኑት ለአንተ አዲስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ቀደም ያልሞከርከውን ነገር እንድትሞክር እናበረታታለን፡፡ ሆኖም ግን አርሶአደሮችን ቀድሞ ያልሞከሩትን ነገር ከአንተ ጋር ለመሞከር ፍላጎት ካሳዩ ሁሉም አብረውህ እንዲማሩት መጠየቁ ጥሩ ሀሳብ ነው፡፡ የመስማማት አዝማሚያቸው ከፍ ያለ ይሆናል፡፡ፈቃዳቸው መጠየቅህን ያደንቃሉ ለለውጡ ሂደትም ታጋሽ ይሆናሉ፡፡

የትክክለኛ አጥኚ ዝንባሌ አስፈላጊነት

ከአርሶ አደሮች ጋር የሚኖርህ ስብሰባ ዓላማው ምንም ይሁን ከእነሱ ጋር በተገናኘህ ቁጥር ከእነሱ ትምህርት እንደምታገኝ አስታውስ ፡፡ በመጀመሪያ ጉብኝትህ ሁሉንም ነገር ለማጠናቀቅ አትጨናነቅ፡፡ ከአርሶ አደሮች ጋር የረዥም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት በመገንባት ላይ ነህ ፡፡ ጥሩ እና ዘላቂ ግንኙነት ለመገንባት አክብሮት እና መረጋጋት አስፈላጊ ናቸው፡፡ ትህትና፣ ክብር፣ ትዕግስት እንዲሁም ገበሬዎች በሚናገሩት እና በሚያሳዩት ነገር ሁሉ ፍላጎትን አሳይ፡፡ ጥሎ በመሄድ ፋንታ እዚያው መቆየትን ምረጥ፡፡ በተረጋጋ እና በትጋት መንፈስ ፤ በማዳመጥ፣ በመመልከት፣ እንዲሁም ሀሳብን ባለማቋረጥ ከመንደርተኞቹ ጋር የተሻለ ትስስር ትፈጥራለህ፡፡

ለሀሳቦቻቸው እና ለሚሰሩት ስራ ክብርን ስታሳይ ተመልሰህ በምትጎበኛቸው ጊዜ በደስታ እንደሚቀበሉህ አያጠራጥርም፡፡ ከጅምሩ ታማኝ እና ግልፅ መሆንም አስፈላጊ ነው፡፡ የጉብኝትህ ምክንያት ከአርሶ አደሮች ጋር ለመገናኘት እና ከእነሱ ግብአት ለማግኘት እንደሆነ ፤ ግብአቱም ለግብርናቸው መሻሻል የሚጠቅም የሬድዮ ፕሮግራም ዝግጅት ለማደራጀት እንደምትጠቀምበት ግለፅላቸው፡፡

አምስት የጥናት ስራዎች

ቀጥሎ የምናያቸው ከአድማጭ ማህበረሰብህ ጋር የምትግባባባቸው እና ምን አይነት የግብርና መረጃዎች እንደሚፈልጉ ለመለየት የሚያግዙህ ፤ በአንፃራዊነት ቀለል ያሉ አምስት መንገዶች ናቸው፡፡

1) የሬድዮ ፕሮግራሞችን እና የሞባይል ስልኮችን ለመረጃ መሰብሰቢያነት ተጠቀምባቸው፡፡

የሬድዮ ፕሮግራሞች
የአርሶ አደሮች የሬድዮ ፕሮግራም ካለህ በፕሮግራሙ ውሥጥ የስልክ ጥሪዎችን በመጠቀም አርሶ አደሮች እየደወሉ በግብርናቸው ዙሪያ በጣም በሚጠቅማቸው ጉዳይ እንዲወያዩ ጠይቅ፡፡

የድምፅ መልዕክት
የድምፅ መልዕክት መቅረጫ ሲስተም በማዘጋጀት አርሶ አደሮች አየደወሉ እንዲሳተፉ ፤ ዋናው ግብርናቸውን ዋስትና ሁኔታቸውን እንዲገልፁ ጠይቃቸው፡፡

የፅሁፍ መልዕክት
ሁለት የፅሁፍ መልዕክት አጠቃቀሞች አሉ፡፡ መጀመሪያ በጣም ግልፅ በሆኑ ጥያቄች ላይ ግብረመልስን መጠየቅ ትችላለህ፡፡ ፕሮግራም አቅራቢዎች ጥያቄዎችን በማቅረብ አርሶ አደሮችን በፅሁፍ መልዕክት እንዲመልሱ ይጠይቃሉ፡፡ በተለያዩ ቀናት የተለያዩ ጥያቄዎችን ማቅረብ ትችላለህ፡፡ ወይም አድማጮች መልሳቸውን በድምፅ የሚያስቀምጡበት ዘዴ ማመቻቸት ትችላለህ፡፡ለምሳሌ አድማጮችህ አዎ ወይም አይደለም በማለት ወይም አይደለም ፣ ሁልጊዜ፣ አንዳንዴ፣ በፍፁም በማለት የሚመልሱት ዓይነት ጥያቄዎችን መጠየቅ ትችላለህ፡፡ የአርሶ አደሮች መልሶችን በቋትህ ውስጥ ጠብቅ፡፡ እንደ ፍሮንትላይን /Frontline SMS/ የተሰኘው የመሳሪያ ዓይነት አቅርቦት ካለህ ሁሉንም የፅሁፍ መልዕክቶችን በኮምፒዩተር ውስጥ ማጠራቀም ትችላለህ፡፡ በእርግጥ የፅሁፍ መልዕክቶች ጠቃሚነት በሞባይል ስልኮች አቅርቦት እና በተጠቃሚዎች የትምህርት ሁኔታ ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ የፅሁፍ መልዕክቶች ይዘት የማህበረሰብህን አርሶ አደሮች ላይወክሉ ይችላሉ፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ስለ ግብርና እና ስለ ሌላ መተዳደሪያ ይበልጥ ሰፋፊ ጥያቄዎችን መጠየቅ ትችላለህ፡፡ ወይም በቀላሉ አድማጮችህን ጣቢያህ በግብርና እና በምግብ ዋስትና ዙሪያ አስፈላጊ የሚሉትን ቢናገሩ ደስተኛ እንደሚሆን አሳውቅ፡፡ ይህ አቀራረብ ታዲያ ውሱን ጉዳይ ማተኮር ላይ ያንሰዋል፡፡ ሆኖም ግን በተለይ ከአድማጭ ማህበረሰብህ ጋር የነበረህ ግንኙነት ውሱን ከሆነ አርሶ አደር አድማጮችህን እንዲሳተፉና ፍላጎታቸውን እንዲገልፁ ለማበረታታት ስኬታማ መንገድ ነው፡፡

2) የአካበቢ ገበያዎችን ጎብኝ

ከተለያዩ አካባቢ እና ማህበረሰቦች የሚመጡ አርሶ አደሮችን ለመገናኘት የአካባቢ ገበያዎች ወሳኝ ቦታዎች ናቸው፡፡ የቡድን ውይይቶችን እና ስብሰባዎችን ለማመቻቸት ልትቸገር ትችላለህ፡፡ ሆኖም ግን ገበያው ላይ ዕቃ የሚሸጡ አርሶ አደሮች የአካባቢያቸውን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ፤ ያሉዋቸው ዕድሎች እና ፈተናዎችን በተመለከተ ጥሩ ምስል ሊሰጡህ ይችላሉ፡፡

3) የአርሶ አደር ተቋማትን አማክር

መደበኛ ስብሰባ ያላቸው የአካባቢ አርሶ አደር ተቋማት ወይም ተባባሪዎች ካሉ ከእነሱ ጋር ተገናኝተህ በአካባቢው ስላለው አስፈላጊ ግብርና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት የምትችልበት ዕድል ሊኖርህ ይችላል፡፡

4) ከአካባቢው የግብርና ኤክስቴንሽን ጋር ተነጋገር

በአካባቢው ባሉት የኤክስቴንሽን አገልግሎቶች አቅም መሰረት ይህ ለአንተ ስለ አርሶ አደር ፍላጎቶች ለማጥናት ጥሩ መንገድ ሊሆንልህ ይችላል፡፡ የተወሰኑ የኤክስቴንሽን ባሙያዎች አርሶአደሮችን ትክክለኛ ፍላጎቶችን ጠንቅቀው የሚያውቁ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ ከአነስተኛ የአርሶ አደሮች ግብርና ጋር ፈፅመው የማይጣጣሙ በቀላሉ የግብርና ሚንስቴር የሚያስቀድማቸው ዝርዝሮችን ብቻ ይዘው ይጓዛሉ፡፡ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ የኤክስቴንሽን ባሙያዎች ፤ ከአርሶ አደሮች ተቋማት እና ከግል አገልግሎቶች ጋር መነጋገርን ከግምት ውስጥ አስገባ፡፡

5) የመስክ ጉብኝቶችን አካሂድ፡፡

ከቡድንህ አባላት ጋር በመሆን በምትደመጥበት አካባቢ አንድ ወይም ሁለት መነደሮችን ጎብኝ፡፡ መንደሮችን ለጉብኝት ስትመርጥ የግብርና ጉዳዮቻቸው ከሰፊው አድማጭህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው መሆናቸውን ከግምት አስገባ፡፡ በመስክ ጉብኝት ጊዜ የኣካባቢው አርሶ አደሮች ቋንቋ መናገር ወሳኝነት አለው፡፡

ማህበረሰብ ውስጥ ለመስራት ምርጫህን ስታደርግ ጉብኝትህን ከማካሄድህ በፊት እንደ ማህበረሰቡ ደረጃ ስብሰባህን አመቻች፡፡ ለምሳሌ ሃላፊዎችን፣ የማህበረሰብ መሪዎችን ማሳተፍ ወይም ቢያንስ ለምታደርገው ስብሰባ ከእነዚህ አመራሮች ይሁንታን ማግኘት ይኖርብሃል፡፡ አነዚህን ባህሎች በጥንቃቄ ስታከብር ከማህበረሰቡ አክብሮትን ታገኛለህ ስራህንም ቀላል ያደርግልሃል፡፡

ከማህበረሰቡ ጋር ለሚደረግ ስብሰባ የተወሰኑ ሃሳቦችን እንይ:

 • ቀላል እና ኢመደበኛ “የዛፍ ስር ስብሰባ”
 • ዓመታዊ፡ በዓመት ሶስት ጊዜ፤ ወርሃዊ ወይም ባጠረ ጊዜ እና መደበኛ የመንደር ውይይቶች ቀረጻ፤
 • በከተማ የአዳራሽ ስብሰባ ወይም የ መሪ ስብሰባ (የዚህ ዓይነት ስብሰባ በተለያዩ አገሮች እና ባህሎች በተለያዩ ስያሜዎች ይታወቃል)

እነዚህ ስብሰባዎች ቀድመው የታቀዱ ሰፋፊ አጀንዳዎች አሉት ፡፡ ለምሳሌ መንደርተኞች የራሳቸውን አስፈላጊ ግብርናዊ ፍላጎቶቻቸውን ለመናገር፤ በራሳቸው ወሳኝ የአኗኗር ጉዳይ ላይ፤ አየር ላይ ማድመጥ ስለሚፈልጉት የመረጃ ዓይነት፤ በግብርና ስራቸው በሚያጋጥሙዋቸው ትልልቅ ችግሮቻቸው ላይ ወይም የሬድዮ ፕሮግራሞች ማህበረሰቡን በተሸለ ደረጃ ማገልገል በሚችልበት ዙሪያ ለመናገር ተዘጋጅተው መጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ ማህበረሰቡን ለስብሰባ እንዲዘጋጅ ስትጠራ ስለ ስብሰባው ይዘትም አብረህ ተወያይበት፡፡

ማህበራዊ ሳይንቲስቶች መረጃ ለመሰብሰብ የተደራጀ መጠይቅ ያዘጋጃሉ፡፡ ይህንን እንድትሞክር ትበረታታለህ፡፡ በተለይም ከማህበረሰብህ ጋር የምትተዋወቅ ከሆነ እና በዚሁ ዓይነት ጥናት ልምዱ ካለህ፡፡ ሶስት ተጨማሪ የጥናት ስራዎችን ተመልከት

በበለጠ ለተደራጀ የአቀራረብ ዝርዝር መመሪያ ተጨማሪ የጥናት ስራዎችን ተመልከት፡፡

የተደራጀ መጠይቅም ተጠቀም አልያም በመጠኑ መደበኛ የሆነ ሰፊ አቀራረብ ውይይቶችህን ከተገለፁት ጥንካሬዎች ፣ ከድክመቶች ከዕድሎች እና ከችግሮች ኣኳያ መተንተን አስፈላጊ ነው፡፡ ይበልጥ የተደራጀ አቀራረብ ጥንካሬዎችን ፣ ድክመቶችን፤ ዕድሎችን እና ችግሮችን ወይም ስጋቶችን የሚመለከቱ በግልፅ የተለዩ ጥያቄዎችን ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች የሚከተሉትን መረጃዎች ለማግኘት የሚዘጋጁ ናቸው፡፡

በግብርና ስኬታማነት አስተዋፅኦ ያደረጉ የአርሶ አደሮች ጠንካራ ጎኖች ለምሳሌ፡-

 • አፈር፣ ዘሮች ፣ እና ሰብሎች ላይ ያላቸው ዕውቀት
 • የግብርና ክህሎታቸው
 • የሰብሎቹ ገበያዎች
 • ያሉዋቸው መሳሪያዎች
 • ያላቸው የሰው ሀይል (ታላላቅ ልጆቻቸው እና ዘመዶቻቸው)

ሶ አደሮች በሙሉ አቅማቸው እንዳይጠቀሙ የገጠሙዋቸው ድክመቶች ለምሳሌ:

 • የመሬት፣ የዘር፣ የውሃ፣ እና የሌሎች ግብአቶች እጥረት
 • በትክክል ለመስራት የሚያስችል ክህሎት ማነስ፡፡
 • ለምርቶቻቸው ገበያ ማነስ
 • በዓመቱ ወሳኝ የስራ ወቅቶች በቂ የሰው ሀይል አለማግኘት፡፡
 • የአፈር መሳሳት፣ ዝቅተኛ የዘር ጥራት፣ ወይም የሰብሎች ለበሽታና ለተባይ መጋለጥ፡፡
 • ድርቅ፤ በተባይ መወረር፤ ጎርፍ፤እና ያልተጠበቁ የዝናብ ወቅቶች
 • የጤና መጓደል፤ ቁስለት፤እና እንዳይሰሩ የሚያደርጉዋቸው ሌሎች ሁኔታዎች

ሴት እና ወንድ አርሶ አደሮች ህይወታቸውን ለማሻሻል ያላቸው ዕድል ለምሳሌ:

 • ኣዳዲስ ሰብሎች እና ገበያዎች
 • የአፈር ለምነት እና የምርታማነት አዳዲስ ዘዴዎች፡፡
 • አዳዲስ የሰብሎች አያያዝ እና የመከላከል ዘዴዎች

አርሶ አደሮችን የሚያጋጥሙዋቸው ችግር እና ስጋቶች፡፡ ለምሳሌ:

 • የአየር ሁኔታ ለውጥ
 • ፖለቲካዊ አለመረጋጋት
 • የገበያ ዋጋ መውረድ ወይም የገበያ ፍላጎት
 • ዘር እና ማዳበሪያ የመሳሰሉ ግብአቶች እጥረት
 • ከመስክ ጉብኝት የምታገኘውን መረጃ የአርሶ አደር ፕሮግራምህን ለማሻሻል ትጠቀምበታለህ

  የእርሻ ጉብኝት
  ከማህበረሰቡ ጋር ስትሆን የግለሰቦችን ማሳዎች ልትጎበኝ ትፈልግ እና አርሶ አደሩን እንዲያሳይህ ልትጠይቀው ትችላለህ፡፡ከማህበረሰቡ ጋር ከመሰብሰብህ በፊት የዚህ ዓይነት ጉብኝት ማድረግ ጥሩ ልምድ ነው፡፡ ስለ ግብርና ወቅቶች አርሶ አደሩን ጠይቀው፡፡ በዓመቱ የተለያዩ ወቅቶች ምን ምን እንደሚያመርት ጠይቀው፡፡ ስለምታያቸው ነገሮች ስለተጠቀማቸው ነገሮች ወደፊት ምን ለውጥ ለማሳየት እንዳቀደ ጠይቅ፡፡

  ሶስት ተጨማሪ ጥናታዊ ስራዎች

  በአድማጮች ጥናት ወይም ስልጠና የበለጠ ልምድ ላላቸውና ከአድማጭ ማህበረሰብ ጋር የተሸለ መደበኛ ግንኙነት ላላቸው በመስክ ጉብኝት ወቅት መረጃ ለመሰብሰብ የሚረዱህ ሶስት ተጨማሪ የተደራጁ አሰራሮች ቀጥለው ቀርበውልሃል፡፡

  1) ለ“ልዩ ቡድን ውይይት ” የአርሶ አደሮች ቡድን አሰባስብ

  የልዩ ቡድን ውይይት ምንድነው? በአመቻች አማካኝነት የሚሰባሰብና በተመረጠ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በነፃነት የሚወያዩበት የሰዎች ቡድን ነው፡፡ የልዩ ቡድን ውይይቶች ሰዎችን የተወሰነ ጥያቄ ላይ መልስ እንዲሰጡ የሚጠይቅ አሰራር ነው፡፡ ጥያቄዎቹ በጣም ሰፋፊም ጠባብም ሊሆኑ የሚችሉ፤ አና ይበልጥ አንድ ጉዳይ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው፡፡

  ከሴት አርሶ አደሮች ጋር ቢያንስ አንድ የትኩረት ቡድን፤ አንድ የወንዶች የትኩረት ቡድን፤ ከተቻለ አንድም ከ ወጣት አርሶአደሮች ቡድን እነዲኖሩህ አቅድ፡፡ ከአዛውንት አርሶ አደሮችም እንደዚሁ መሰብሰብ ሊኖርብህ ይችላል፡፡ ለእነዚህ ውይይቶች የተወሰኑ ቁልፍ የሆኑ ጥያቄዎችን አዘጋጅ፡፡ ከእያንዳንዱ ቁልፍ ጥያቄ ቀጥሎ በተሳታፊዎች በሚሰጡት ምላሽ መሰረት የክትትል ጥያቄዎችን አቅርብ፡፡ እያንዳንዱ የቡድኑ አባል መናገር መቻሉን አረጋግጥ፡፡ አንተ ጥሩ ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ እንድታተኩር እና መልሶቻቸውንም በጥንቃቄ እንድታዳምጥ ከቡድን አባላትህ አንዱን ዝርዝር ማስታወሻ እንዲይዝ እና የውይይቱን በመቅረፀ ድምፅ እንዲይዝ ጠይቅ፡፡
  ቀጥለን የምናያቸው ምሳሌዎች ውይይቶችህን ለማስጀመር እና ለመምራት የሚረዱህ የተወሰኑ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ አርሶ አደሮች ለምን ምላሾቻቸውን እንደሰጡ ለይቶ ማወቅ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አስታውስ፡;ሆኖም ውይይቱን በምታመቻችበት ጊዜ “ለምን” የሚለውን ቃል እንዳትጠቀም ለምን የሚለውን መፈለግ የአንተ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን ለይተህ ማወቅ ያሉበትን ሁኔታ እንድታውቅ ይረዳሃል፡፡

  ጥያቄዎች (ስለ ጥንካሬዎች): በዚህ ሰዓት ለእርስዎ በግብርና ላይ ጥሩ ስራ መስራት ምንድነው? እባክዎን እንዴት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንደሚገኝ ይግለፁ፡፡ “እባክዎን ተጨማሪ ማብራሪያ ያድርጉልኝ” ወይም “እባክዎን ይግለፁልኝ” (እነዚህ ለበለጠ ዝርዝር የሚቀርቡ ጥያቄዎች በጥንካሬ፣በድክመቶች ፣ በመልካም አጋጣሚዎች፣ እና በፈተናዎች ወይም ስጋቶች ዙሪያ እንደ መከታተያ ጥያቄዎች መጠቀም ይቻላል፡፡)

  ምላሾችን መሰረት በማድረግ የክትትል ጥያቄዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡

  • ምን ሰብል /እንስሳ ነው የላቀ ስኬት እያስገኘልዎ ያለው?
  • እንደ አርሶ አደር የትኛው ስራ ላይ የተሸልኩ ነኝ ይላሉ?
  • ለግብርና ስራህ የሚረዱህ ምን ምን አቅርቦቶች እና መሳሪያዎች አሉዎት?
  • ለግብርና ስራዎ ከጎንዎ የሚረዳዎት ማን አለልዎት ?

  ጥያቄዎች (ስለ ድክመቶች): በአሁኑ ወቅት በግብርናህ ላይ እየጠቀመኝ አይደለም የሚሉት ነገር ምንድነው ? እባክዎን ያብራሩልኝ

  የክትትል ጥያቄዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡

  • ምን ሰብል /እንስሳ ናቸው ችግር እየፈጠሩባቸው ያሉት ? እንዴት ?
  • ለማግኘት ከባድ የሆኑብዎት ግብአቶች የትኞቹ ናቸው ?
  • እያጡ ያሉት መረጃ ወይም ዕውቀት አለ ?

  ጥያቄዎች (ስለ መልካም አጋጣሚዎች): ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉና በግብርና ስራዎችዎ ሊጠቅሙዎት የሚችሉ ነገሮች አሉ ? እባክዎን ያብራሩልኝ

  የክትትል ጥያቄዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡

  • ሊረዳዎት የሚችሉ ማናቸውም አዳዲስ የመንግስትአገልግሎቶች/ድጎማዎች/ወይም ፖሊሲዎች አሉ?
  • ሊረዳዎት የሚችሉ አዳዲስ መንግስታዊ ያልሆኑ ፕሮጀክቶች አሉ ?
  • ሊረዱዎት የሚችሉ አዳዲስ የገበያ ዕድሎች አሉ?

  ጥያቄዎች (ስለ ፈተናዎች/ስጋቶች ): ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉና እንደ አርሶ አደር በግብርና ስራዎችዎ ሊጎዳዎት የሚችሉ ነገሮች አሉ ? እባክዎን ያብራሩልኝ

  በመልሱ መሰረት የክትትል ጥያቄዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡

  • ወደፊት መሬትዎን አጣዋለሁ የሚል ስጋት አለዎት?
  • የአየር ሁኔታ መቀያየር ያሳስቦታል ?

  አርሶ አደሮች ስለ ሚሸጡዋቸው ሰብሎች ከገበያ ዋጋዎች ጋር እንዴት እንደሚተሳሰሩ ማወቅም አስፈላጊ ነው፡፡ የዋጋ ሰንሰለት “value chain” በግብርና አገላለፅ እንደ በቆሎ፣ አትክልት ወይም ጥጥ ያሉ መሰረታዊ የግብርና ውጤቶች በማሳቸው በማምረት፣በማሰናዳት፤ በማሸግ እና በማሰራጨት ደረጃዎች አልፈው ወደ ደንበኞች የሚያመጡ ሰዎች እና ስራዎች ናቸው፡፡

  ጥያቄዎች (ስለ ገበያ ትስስር /value chain/): አርሶ አደሮችን ሰብሎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ወይስ የተወሰነውን ይሸጣሉ የሚለውን ጠይቅ

  የክትትል ጥያቄዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡

  • የት ነው የሚሸጡዋቸው? ለማን?
  • የአርሶ አደሮች ህብረት አካላት ናቸው?
  • በሚቀበሉዋቸው ዋጋዎች ይረካሉ?
  • ሰበሎቻቸው በማሳቸው ላይ እሴት ይጨምሩባቸዋል? በህብረቱ በኩል?
  • እነሱ ወይም ህብረታቸው እሴት የተጨመረባቸው ውጤቶችን ይሸጣሉ? ለቸርቻሪ? ለአምራች?
  • ግብአቶችስ? ግብአቶችን የሚገዙት የት ነው? በሚከፍሉትስ ዋጋ ደስተኛ ናቸው?
  • ከገበያ ትስስሩ ጋር ባላቸው ግንኙነት ደስተኞች ናቸው ? በፍትሃዊነት እንስተናገዳለን ብለው ያምናሉ?

  2) መሸጋገሪያ መንገድ

  ይህ መሸጋገሪያ መንገድ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ከአንዱ ወደ ሌላው የህበረተሰቡ አቅጣጫ በምትራመድበት ጊዜ በአንተ እና በበርካታ የአካባቢው አርሶ አደሮች መካከል የሚደረግ ውይይት ነው፡፡ ከመልከዓ ምድር እና ከሚኖረው ከፍተኛ ስብጥር እና ከግብርና አኳያ መንደርተኞቹን የትኛው መንገድ መምረጥ እንዳለብህ ጠይቅ፡፡ የአንተ ስራ መታዘብ፣ ማዳመጥ፣ እና ስለምታየው እና እያለፍክበት ስላለው ቦታ ጥያቄዎችን መጠየቅ ነው፡፡

  አርሶ አደሮች ማንኛውንም የሚፈልጉት ነገር እንዲገልፁ ጠይቃቸው፡፡ሆኖም በሚቀጥሉት ይዘቶች ብቻ እንዳይወሰኑ፡-

  • በሚያበቅሉዋቸው ሰብሎች ወይም በሚያሳድጓቸው እንስሳት
  • የግብርና ስራን በሚያከብዱባቸው ወይም በሚያቀሉላቸው መልከዓ ምድራዊ አቀማመጦች (ለምሳሌ ተራራማ ቦታዎች የመሬት መሸርሸርን ያባብሳል እንዲሁም ወንዝ ደግማ ለመስኖ ሊጠቅማቸው ይችላል፡፡); እና
  • የጋራ እና ጥብቅ ቦታዎች፡፡

  ብዙ ጥያቄዎች መጠየቅህን አረጋግጥ፡፡ ለምሳሌ የሚቀጥሉትን መጠየቅ ትችላለህ :

  • ወንዶች ወይም ሴቶች አንድ ዐይነት ሰብል ካበቀሉ፤/li>
  • መሬቱ በማን ስም መሆኑን፤/li>
  • የትኞቹ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ አበላት የግብርና ጉዳዮችን እንደሚወስኑ፤/li>
  • ሰብሎችን እንዴት እንደሚያቀያይሩ

  ምን እንደተጎበኘ እና እየተካሄደ ያለውን ውይይት በማስታወሻ የሚይዝልህ አንድ ሰው ይኑርህ

  3)“የደረጃ አሰጣጥ ” ልምምድ

  ከ8-10 አባላት ላሉት የአርሶ አደሮች ቡድን እንደ አርሶ አደሮች ለግብርና ስራቸው ሊረዱዋቸው የሚችሉ የመረጃዎች ዝርዝር እንዲያዘጋጁ ጠይቅ ፡፡ ዝርዝሩ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል ፡

  • የአካባቢ እና የክልላዊ ገበያዎች የገበያ ዋጋ፤
  • የአካባቢ የአየር ሁኔታ ዘገባዎች፤
  • የዘር መረጃዎች፤
  • የአፈር ለምነት ማሻሻያ መረጃዎች፤
  • የተሰበሰቡ ምርቶች አዘገጃጀት እና አያያዝ፤ እና
  • የገበያ አማራጭ መረጃዎች፡፡

  ዝርዝሮቹን ከ4-6 የመረጃ ዓይነቶች እንዲሆኑ አድርገህ ለመመደብ ሞክር፡፡ በመቀጠል ቡድኑ አንድ ላይ ሆኖ ዝርዝሮቹን በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ጀምሮ ወደታች እንዲመድቡ ጠይቅ፡፡ ከአርሶ አደሮቹ ጋር በመሆን የተለያዩት መረጃዎቹን የሚወክሉ ቁሶችን ምረጥ ፡፡ ቀጥሎ ለአርሶ አደሮቹ ሃያ ድንጋዮችን በመስጠት እንደ ቡድን የትኞቹ ዓይነት መረጃዎች በጣም አስፈላጊ ፤ የትኞቹ ዓይነት አነስተኛ ጠቃሚነት እንዳላቸው እንዲመድቡ አድርግ፡፡ ይህን ተጨማሪ ድንጋዮችን በጣም አስፈላጊ ካሉዋቸው የመረጃ ዓይነቶች ቀጥሎ በማስቀመጥ በሌሎቹ አጠገብ ደግሞ አነስተኛ የድንጋይ ቁጥሮችን በማስቀመጥ ሊሰሩት ይችላሉ፡፡

  ቡድኑ የራሱን ውሳኔ እንድወስን በቂ ጊዜ ስጥ፡፡ አርሶ አደሮቹ የመጨረሻ ውጤት ላይ እስኪደርሱ ድንጋዮቹን ለበርካታ ጊዜ ከአንዱ የመረጃ ዓይነት ወደ ሌላኛው ሲያመላልሱ ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ፡፡ በጠንቃቄ አዳምጥ አናም አርሶ አደሮቹ የትኛው መረጃ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ለመወሰን የሚያደርጉትን ውይይት በማስታወሻህ ያዝ፡፡ በማዳመጥ የትኛው የመረጃ ዓይነት ከሌላኛው ይልቅ ለምን በጣም ጠቃሚ እንዳሉት ትማራለህ፡፡

  ቀጥሎ የቀረበው ሰንጠረዥ አርሶ አደሮች አራት የተለያዩ ዓይነት መረጃዎችን እንዴት እንደመደቡዋቸው አንድ ማሳያ ምሳሌ ነው፤

  ክፍል II: አድማጮችህን ማወቅ

  የዚህ መረጃ ሁለተኛው ክፍል የአድማጮችህን ባህርያት ፤የእርሻ መጠን፤ የቤተሰብ መጠን፤ ዋና ሰብሎችና ከብቶች የመሳሰሉ ነገሮችን እንዴት መወሰን እንደምትችል የተወሰነ ሀሳብ ይሰጣል፡፡

  እነዚህን መረጃዎች ስታገኝ አድማጮችህን እንድትገልፃቸው ሊረዱህ ይችላሉ፡፡ ቀጥሎ የግብርና ዝግጅት አድማጮች ሊሆኑ የሚችሉ የተወሰኑ ክፍሎችን እንይ፤ ወንድአርሶ አደሮች ፤ ሴት አርሶ አደሮች : ቡና አባቃዮች ፤አነስተኛ አአርሶ አደሮች ፤ ወጣት አርሶ አደሮች ፤ የንግድ አርሶ አደሮች ፤ በ 14 እና 25 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች፤ የሁለተኛ ደረጃ ትህርት ቤት ተማሪዎች ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ያላጠናቀቁ ተማሪዎች የአድማጭነት ዕድሉ መጨረሻ የለውም፡፡

  ፕሮግራምህን እንዲያደምጡልህ የምትፈልጋቸው አድማጮች ሁኔታ የሚወሰነው በማህበረሰቦቹ ባህርይ እና በሬድዮ ጣቢያህ በሚሰራጩ የግብርና ስራ ዓይነቶች ነው፡፡ ከሚያዳምጡህ ማህበረሰቦች ጋር ስትጎበኝና ስትገናኝ የዚህ ዓይነት ሀሳብ ለማግኘት ልትሞክር ትችላለህ፡፡

  ቀጥሎ አድማጮችህ እነማን እንደሆኑ ለመለየት (ለመግለፅ) የሚረዱህ ሁለት የጥያቄ ምድቦችን እናያለን፡፡ ለእነዚህ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልሶች እና ጥክክለኛ የቁጥር መረጃ የማግኘት ዕድልህ አነስተኛ ነው ፡፡ ሰለዚህ የራስህ የተሻሉ ግምቶችን ለማግኘት የራስህ ጥያዌዎች ማዘጋጀት ይኖርብሀል፡፡

  ቀጥለው ስለተዘረዘሩት ሁሉም ጥያቄዎች መረጃ ላታገኝ ትችላለህ፡፡ አትጨነቅ ዋናው ነገር ስለነዚህ ዓይነት ጥያቄዎች ማሰብ እና በተቻለ መጠን ትርጉም ያላቸው መልሶችን ለማግኘት መሞከር ነው፡፡

  የስነ ህዝብ መረጃ (ስለ ሰዎች እና ስራዎቻቸው መረጃ):

  • ምን ያህሉ (ለምሳሌ፡ አንድ ሩብ ፤ አንድ ግማሽ ፤ ሶስት ሩቦች፤ 95%) አዋቂ አድማጭህ በሰብል ምርት ወይም በእንስሳት እርባታ ሙሉ በሙሉ ይተዳደራሉ?
  • አማካኝ የእርሻ መጠን ምን ያህል ነው ?
  • በ ግብርና ቤተሰብ ውስጥ በአማካኝ ምን ያህል ሰዎች አሉ?
  • በአነስተኛ ግበብርና የተሰማሩ የአርሶ አደሮች ሽፋን ምን ያህል ነው?
  • በከፍተኛ ወይም በንግድ ግበብርና የተሰማሩ የአርሶ አደሮች ሽፋን ምን ያህሉ ነው?
  • የግብርና ቤተሰቦች አማካኝ ገቢ ምን ያህል ነው?
  • በአካባቢህ የድርቅ / የረሃብ ወቅት አለ? ከሆነ መቼ?
  • በድርቁ ወቅት ቤተሰቦች እንዴት ነው የሚቋቋሙት?
  • የገጠር ቤተሰቦች ጥሩ የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎቶች ያገኛሉ?
  • ገበያ ላይ ምንም የማይሸጡ ለራሳቸው ምግብነት ብቻ የሚያመርቱ የገጠር ቤተሰቦች ምን ያህሉ ናቸው ?
  • የገቢ ምንጫቸው ገበያ ላይ የተመሰረተ የገጠር ቤተሰቦች ምን ያህሉ ናቸው?
  • ምን ያህሉ የገጠር ቤተሰቦች ከግብርና ውጪ ሌሎች የገቢ ምንጮች ያሉዋቸው ምን ያህሉ ናቸው ?
  • በአካባቢህ የሚበቅሉ ዋና ዋና ሰብሎች እና የሚራቡ የእንስሳት ዓይነት ምን ምን ናቸው?
  • ከወንዶች በተለየ ሴት አርሶ አደሮች ምን ምን ይሰራሉ?
  • ምን ያህሉ ወጣቶች ናቸው ግብርና ላይ የተሰማሩት?
  • ምን ያህሉ የገጠር ወንዶች የተማሩ ናቸው ?
  • ምን ያህሉ የገጠር ሴቶች የተማሩ ናቸው ?

  ስለ ሬድዮ ተደራሽነት ጥያቄዎች

  • ምን ያህሉ ወንድ አርሶ አደሮች በቤታቸው ሬድዮ አላቸው?
  • ምን ያህሉ ሴት አርሶ አደሮች በታቸው ሬድዮ አላቸው?
  • ሬድዮ ጣቢያህ ማሰራጫህ ባለበት የስርጭት ክልል ውስጥ በሁሉም ሰው ሊደመጥ ይችላል?
  • ምን ያህሉ ወንድ አርሶ አደሮች የሬድዮ ፕሮግራሞችን በቡድን ያዳምጣሉ?
  • ምን ያህሉ ሴት አርሶ አደሮች የሬድዮ ፕሮግራሞችን በቡድን ያዳምጣሉ?
  • ወንድ አርሶ አደሮች የሚወዱዋቸው የሬድዮ ፕሮግራሞች ምንድናቸው?
  • ሴት አርሶ አደሮች የሚወዱዋቸው የሬድዮ ፕሮግራሞች ምንድናቸው?
  • ወጣት አርሶ አደሮች የሚወዱዋቸው የሬድዮ ፕሮግራሞች ምንድናቸው?
  • ጎልማሳ አርሶ አደሮች የሚወዱዋቸው የሬድዮ ፕሮግራሞች ምንድናቸው?
  • እነዚህ ፕሮግራሞች ለምን ታዋቂ እንደሆኑ ግለፅ፡፡
  • ወንድ አርሶ አደሮች የግብርና መረጃዎችን ከሬድዮ ያገኛሉ? ከሆነ የትኞቹ ጣቢያዎች እና የትኞቹ ፕሮግራሞች?
  • ሴት አርሶ አደሮች የግብርና መረጃዎችን ከሬድዮ ያገኛሉ? ከሆነ የትኞቹ ጣቢያዎች እና የትኞቹ ፕሮግራሞች?
  • ቤተሰቦች የግብርና መረጃዎችን ለማግኘት ሬድዮ ለማዳመጥ የሚመርጡት ሰዓት የትኛው ነው?
  • ወንድ አርሶ አደሮች የግብርና መረጃዎችን ለማግኘት ሬድዮ ለማዳመጥ የሚመርጡት ሰዓት የትኛው ነው?
  • ሴት አርሶ አደሮች የግብርና መረጃዎችን ለማግኘት ሬድዮ ለማዳመጥ የሚመርጡት ሰዓት የትኛው ነው?

  እንደነዚህ ዓይነቶች በርካታ ጥያቄዎችን ልታስብ ትችላለህ፡፡ የእነዚህ ጥያቄዎች መልሶች የአርሶ አደር ፕሮግራም አድማጮችህን ለመግለፅ ሊረዱህ ይገባል፡፡

  አድማጮችህን ስትገልፅ አንድ የተለየ ጉዳይ ላይ ማተኮር እንዳለበህ አስታውስ፡፡ የምትፈልጋቸው አድማጮች ሁሉም አርሶ አደሮች፣ ወንዶች፣ ሴቶች፣ ከ10-80 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ከ 0.5-100 ሄክታር መሬት ያላቸው ሰዎችን ላያካትት ይችላል፡፡ የዚህ በጣም ትልቅ እና የተሰባጠረ ቡድን ፍላጎቶች እና የግብርና ተመኩሮዎችም እንደ ፕሮግራም አቀራረብ ምርጫቸው በጣም በርካታ ይሆናሉ፡፡ ሆኖም ግን አንድ አካባቢ ያሉ በርካታ አነስተኛ አርሶ አደሮች አስፈላጊ የጋራ ጉዳዮች ይኖራቸዋል፡፡ የአርሶ አደር ፕሮግራምህ አብዛኛውን ጊዜው በእነዚህ የጋራ ጉዳዮች ላይ ማዋል አለበት፡፡በተጨማሪም ለተወሰነ የአርሶ አደር የማህበረሰብ ክፍል ብቻ የሚጠቅሙ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚሸፍኑ ፕሮግራሞችን መፍጠር ይኖርበታል፡፡

  በሚያሳዝን አጋጣሚ ሴቶች የግብርና ፕሮግራም ማዳመጥ የሚፈልጉት እራት የሚዘጋጅበት ሰዓት ላይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሬድዮውን የሚያገኙበት ሰዓት ያኔ ብቻ ሰለሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ወንዶች በዛ በቀን እውጭ ይዝናኑበታል፡፡ ስለዚህ ሁለቱንም ፆታዎች አንድ ላይ ከግምት በማስገባት ፕሮግራምህን ማሰራጨት ጥሩ ሀሳብ አይደለም፡፡ አልያም በተለያዩ ሰዓታት በተደጋጋሚ በማሰራጨት ሁሉንም ቡድኖች ለመዳረስ ሞክር፡፡

  ማጠቃለያ

  አድማጮች ጥናት ቀጣይ ሂደት መሆኑን አስታውስ ፡፡ ለተወሰኑ የመረጃ ዓይነቶች ፍላጎት እንደሚኖራቸው ሁሉ አድማጮችህ በጊዜ ሂደት ይቀየራሉ፡፡ ስለዚህ በመከባበር ላይ የተመሰረተ፤ ግንኙነት መመስረት ወሳኝ ነው፡፡በማህበረሰቡ ስትገኝ ሙሉ በሙሉ መረጃ ለመሰብሰብ እንዳልሆነ እና ዋናው ተልዕኮህ አድማጭ ማህበረሰብህን ማገልገል መሆኑን አስታውስ፡፡

  ምስጋና

  አስተዋፅኦ ያበረከቱ : ቪጄ ኩድፎርድ፣ ማኔጂንግ ኤዲተር፤ ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል፣ ሰነዶችን በመመርኮዝ በዶዋግ ዋርድ፣ የፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ሊቀመንበር ፤ ብላይት ሚካይ፣ የፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ማኔጀር፣ የ አዘጋጆች ምንጮች፣ ፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል እና ዴቪድ ሞውበሬይ፣ የፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል የስልጠና እና የደረጃዎች ማኔጀር

  ገምጋሚ: ዶዋግ ዋርድ፣ የፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ሊቀመንበር

  ይህ ፕሮጀክት የካናዳ መንግስት የፋይናንስ ድጋፍ በካናዳ ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ኤጀንሲ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ የሚሳለጥ ነው፡፡
  ይህ ሰነድ ወደ አማርኛ የተተረጎመው በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለስቴፕልስ ፕሮጀክት በሰጠው ድጋፍ ነው