የጊዜ እጥረትን ጨምሮ በገንዘብ ወይም የሎጂስቲክስ ምክንያቶች የራዲዮ ጋዜጠኞች ቃለ መጠይቅ የሚያደርጉላቸውን ሰዎች በአካል ለማግኘት ሊቸገሩ ይችላሉ፡፡ ጥሩው ነገር ግን አሰራጮች ከአርሶ አደሮች ወይም የግብርና ባለሙያዎች ጋር ቃለ መጠይቅ ለማድረግ፣ የሚሠሩ ታሪኮችን በተመለከተ ስብሰባ ለማድረግ፣ ቀጥታ በሚተላለፉ ወይም አስቀድመው በተቀረጹ የራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ የፓነል ውይይት ለማድረግ፣ የማሕበረሰብ አድማጭ ቡድኖችን ለመሰብሰብ እና ሌሎችንም የስርጭት ሥራዎች ለመሥራት መጠቀም የሚያስችሏቸው ብዙ የበይነመረብ መሳርያ ስርአቶች አሉ፡፡

Read More