ባለሙያዎችን ቃለ መጠይቅ ማድረግ : ምርጥ ተሞክሮዎች ለአዘጋጆች እና ለባለሙያዎች

መግቢያ

የባለሙያዎች ቃለ መጠይቅ በግብርና ሬድዮ ፕሮግራምህ ላይ ብዙ ነገሮችን ይጨምርልሃል፡፡ ለአድማጮችህ አስተማማኝ መረጃን ከታማኝ ምንጮች ይሠጥልሃል፡፡ አንዳንድ አርሶ አደሮች ባለሙያ መሆናቸውንም አትዘንጋ፡፡

ይህ የአዘገጃጀት መመሪያ ለአዘጋጆች እና ለባለሙያዎች እንደሚያገለግል አስታውስ፡፡ ምክንያቱም ለሁለቱም ቡድኖች ሌላው የቃለ መጠይቅ ተሳታፊ ያለበትን ድርሻ እና ባህርይ ማወቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡

ውጤታማ የባለሙያዎች ቃለ መጠይቅ አድማጮቼን የበለጠ ለማገልገል በምን መልኩ ይረዳኛል ?

  • አድማጮቼ በጣም ተገቢ እና ወቅታዊ መረጃ ማግኘታቸውን ያረጋግጣል፡፡
  • ከጥናታዊ እና ቴክኒካዊ መረጃ አኳያ ወይም ጠቃሚ ባህላዊ ዕውቀት አኳያ የአድማጮችን ዕውቀት እና ልምድ ያጠናክራል፡፡
  • ውጤታማ የግብርና ልምዶችን በመተግበራቸው አድማጮች በራስ የመተማመን ስሜትን ይፈጥርላቸዋል፡፡ ወይም ስኬታማ ያልሆኑ ልምዶችን እንዲለውጡ ይረዳቸዋል፡፡
  • አድማጮች አዲስ ዕውቀት እና ልምድ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል፡፡
  • አድማጮች የኤክስቴንሽን ሃላፊዎችንና እና ሌሎች ባለሙያዎችን በማህበረሰቦቻቸው ውስጥ እንዲያናግሩ ያበረታታል፡፡

በምን መልኩ የተሻለ ፕሮግራም እንዳዘጋጅ ይረዳኛል ?

  • በሬድዮውን እና በባለሙያ ቡድኖች መካከል ህብረትን ያበረታታል፡፡
  • ባለሙያዎች በመደበኛነት በሬድዮ ፕሮግራሜ ተሳትፎ እንዳላቸው ያረጋግጥልኛል፡፡
  • እንዴት እጀምራለሁ ?

    1. ተዘጋጅ
    2. መጀመሪያዎች እና መውጫዎች
    3. አክብሮት ይኑርህ
    4. ጥሩ የቃለ መጠይቅ ቴክኒኮችን ተጠቀም፡፡
    5. ቃለ መጠይቅ ከባለሙያ ጋር እና ከ አርሶ አደሮች ጋር ምን ልዩነት አለው?
    6. የፍላጎት መጋጨት ፤ በዕውቀት ያለ የተለያየ እይታ፤

    7. ችግሮችን መፍታት
    8. ጥሩ ቃለ መጠይቅ እንዳይኖር የሚያደርጉ ኋላ ቀር ባህሎች እና ሌሎች ዓይነቶች እንቅፋቶችን ማስወገድ፡፡
    9. ወንዶች ሴቶችን ፤ሴቶች ወንዶችን ቃለ መጠይቅ ማድረግ፤
    10. ግንኙነትን ገንባ

    ዝርዝር

    1. ተዘጋጅ

    ለቃለ መጠይቅ አድራጊው:

    • የቃለመጠይቁን ርዕስ እና ሽፋንን ወስን፡፡ ለምሳሌ:
      • “ዛሬ ደሮዎችን ነፍሳትን ስለመመገብ እናወራለን፡፡ ጥቅም ላይ ስለዋሉ የተለያ ዓይነቶች ነፍሳት ፤ በብዛት የተለመደ ዓይነት አጠማመድ እና አረባብ ፤ እንዲሁም ለአርሶ አደሮች ያለውን ጠቀሜታ እና ፈተናን እንዳስሳለን፡፡”
    • ቃለመጠይቅህ ባለሙያው የሚገኝበትን ምቹ ሰዓት ላይ እንዲሆንልህ አስቀድመህ ፕሮግራም በመያዝ የሚወስደውንም ጊዜ አሳውቅ ፡፡
    • በርዕሱ ላይ በጣም አስፈላጊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖርህ አስቀድመህ የተወሰነ ጥናት አድርግ፡፡ የኤክስቴንሽን ወኪልን እያነጋገርክ ከሆነ አስቀድመህ ከተወሰኑ አርሶ አደሮች ጋር ቃለ መጠይቅ በማድረግ አርሶ አደሮች እንዲመለሱላቸው የሚፈልጓቸው ለባለሙያው የምታቀርባቸው ጥያቄዎችን ለመያዝ ሞክር፡፡
    • ቃለመጠይቅ ስለምታደርግለት ባለሞያ እና ስለሞያ መስኩ በትንሹ ጥናት አካሂድ፡፡
    • በእጅህ ባለው ይዘት ላይ እንዲያተኩርልህ ለማድረግ ጥያቄዎችህን በጥንቃቄ አዘጋጅ፡፡
    • ካልሆነ ባለሙያው ቃለመጠይቁን በመቆጣጠር ከያዝከው ርዕስ ጋር የማይዛመድ ይዘት ላይ ሊያተኩር ይችላል፡፡
      ቃለመጠይቅ የሚደረግለት ሰው ቃለ መጠይቁ እንደሚቀረፅ እና አየር ላይ ሊውል እንደሚችል አስቀድሞ ማወቁን እርግጠኛ ሁን፡፡
    • ባለሙያው አድማጮቹ እነማን እንደሆኑ ማወቁን አረጋግጥ፡፡ ለምሳሌ፡- ዓመታትን በትምህርት ቤት ያላሳለፉ እና ቴክኒካዊ ቃላት የበዙበትን መልዕክት ላይረዱ የሚችሉ አነስተኛ የካሳቫ አምራች አርሶ አደሮች ፤በአንፃሩ ደግሞ ቴክኒካዊ ባልሆነ ቋንቋ የተነገረን መልዕክት በሚገባ የሚረዱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
    • አዘጋጅ የጥያቄዎቹን ዝርዝር ቃለመጠይቅ ለሚያደርግለት ባለሙያ አስቀድሞ መላክ አለበት? ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ይህንን ማድረግ እንዳለባቸው ቢሰማቸውም የተወሰኑ ደካማ ጎኖች እንዳሉትም መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የጥያቄዎቹን ዝርዝር በሙሉ ለባለሙያው አስቀድሞ መስጠቱ ባለሙያው ቃለመጠይቁን እንዲቆጣጠረው እና የትኛው ጥያቄ እንደሚከተል እና እንደሚመለስ ስለሚያውቅ በራሱ ፍላጎት ብቻ ለመግለፅ እንዲዘጋጅ ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ለጥያቄዎቹ በየተራ በመመለስ ፈንታ (አድማጮች ደረጃ በደረጃ እንዲያውቁ ለማስቻል) ባለሙያው አንደኛውን ጥያቄ ከመለሰ በኋላ የሌሎች በርካታ ጥያቄዎች መልስም አብሮ ወደ ማብራራት ይገባል፡፡ በዚህ ሁኔታ ታዲያ አዘጋጁ በዝርዝር ለመከታተል እና በእያንዳንዱ ጥያቄዎች ላይ ጥልቀት ያለው መረጃ እናዳያገኝ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ አዘጋጁ አስቀድሞ ባለሙያውን ማሳወቅ ቢችል ተመራጭ ነው፡፡ (ለምሳሌ፡- ለቃለመጠይቅ ፕሮግራም ለመያዝ በሚደውልበት ጊዜ) ውይይት ስለሚደረግበት ርዕስ ፤ እንዲሁም ባለሙያው ሊጠብቃቸው የሚችላቸውን ጥቂት ጥያቄዎችን መስጠት፡፡ በዚህ ፕሮግራም የማስያዝ ውይይትህ ባለሙያው በተቻለ መጠን ጥያቄዎችህን በቀጥታ ሳትገልፅ ስለሚጠየቀው ርዕሰ ጉዳይ በዝርዝር አውራው፡፡

    ለባለሙያው:

    • ከጉዳዩ ጋር ቀጥታዊ ትስስር ያላቸው እውነታዎችን እንዲያውቅ እና በራስህ እንድትተማመን የቃለ መጠይቁን ርዕስ በሚገባ አጥና ፡፡
    • ቃለመጠይቅ ከመጀመርህ በፊት መቆራረጥን ለመቀነስ ስልክህን አስቀድመህ ዝጋ፡፡
    • በቃለ መጠይቅ ወቅት የተዘጋጁ ጥያቄዎች ባይኖርህም እንኳ መንዛዛትን ለመከላከል በተወሰኑ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ እይታህን እጥር ምጥን ባለ መልኩ ግልፅ አድርገህ መፃፍ ሊያስፈልግህ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን መልሶችህን እንዳለ በገለፃ መልኩ ማንበብ ለሬድዮ ጥሩ አይሆንም ፡፡ ቃለ መጠይቅ እንደ ጭውውት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ መልሶችን እንደ አጠያየቃቸው እና በጭውውት መልኩ መመለስ አለባቸው፡፡
      • ለምሳሌ፡- በ ዩጋንዳ አንድ ባለሙያ ፆታ ነክ ጉዳዮች ላይ ከሙዝ ጋር ተያይዞ ባሉት ኣባባሎች ትልልቅ ነጥቦችን በዝርዝር በመያዝ ለቃለ መጠይቅ ሊዘጋጅ ይችላል፡፡ 1) ያገባች ሴት የሙዝ ምርትን መሰብሰብ አይጠበቅባትም ፡፡ ምክንያቱም እንደ ሌባ ልትቆጠር ትችላለች፡፡ 2)ሴቶች ለጭማቂ የሚሆን ሙዝ እንዲሸጡ አይፈቀድላቸውም 3) ሴቶች የሙዝ እርሻ ባለቤት መሆን አይችሉም፡፡
    • ማስታወሻ: ርዕስ የመምረጥ እና ቃለመጠይቁን የመምራት ሃላፊነት ሁሌም የአዘጋጁ ነው፡፡ ምክንያቱም ለአድማጮቹ የሚፈልጉትን መረጃ የማቅረብ ሃላፊነት ያለበት እና የፕሮግራሙን ዓላማ የሚያውቀው አዘጋጁ ስለሆነ ነው፡፡

    2. አጀማመር እና አፈፃፀም

    ለቃለ መጠይቅ አድራጊው :

    አጀማመር :

    • ባለሙያውን ከዚህ ቀደም ቃለመጠይቅ ካደረግክለት በባለፈው ቀረፃ ስለነበረህ ቃለ መጠይቅ ጠቃሚ እንደነበረ አስታውሰው፡፡ ይህን ካላደረግክ ከአድማጮችህ ካገኘሃቸው ግብረመልሶች አካፍል፡፡
    • መናገር ከመጀመርህ በፊት ፍት ለፊታቸው ፈገግታህን በማሳየት መልካም የግንኙነት ስሜት ፍጠር፡፡ከዚያም በትክክል አስተዋውቃቸው፡፡
    • በቀረፃ ወቅት እና የቀጥታ ስርጭት ቃለ መጠይቅ በምታደርግበት ጊዜ ስለ ቃለ መጠይቁ በጥሩ ሁኔታ አስተዋውቃቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ባለሙያውን ስለምትጠይቀው ችግር ፤ በአከባቢው ስለሚኖረው ተፅዕኖ እና ችግሩ ላይ ያለው ተሞክሮ በተመለከተ ለአድማጮችህ በግልፅ አብራራ፡፡ ቀጥለህ ቃለመጠይቅ የምታደርግላቸው ባለሙያዎችን ከሚነሳው ችግር ጋር ያለቸው ሙያዊ ትስስር እና ዝርዝር መረጃ እንደምትጠብቅ ግለፅለት፡፡ለምሳሌ፡-
      • "እየተለዋወጠ ያለው የአየር ሁኔታ በተለይ በደረቁ የክልላችን አከባቢዎች የሚኖሩትን አርሶ አደሮችን ከፉኛ መጉዳቱን ቀጥሏል፡፡ እየተለዋወጠ ካለው የአየር ሁኔታ አኳያ አርሶ አደሮች ማድረግ ያለባቸው ነገር ምንድነው ? የአየር ሁኔታ መዛባት በሰብሎች ላይ በሚያደርስው ተፅዕኖ ላይ ባለሙያ ሚስተር ጆን ፊሪ ከእኛ ጋር ናቸው፡፡ ሚስተር ፊሪ ከዘዴዎቹ የተወሰኑትን በማብራራት ይረዱናል፡፡"

    አጨራረስ :

    • ስለ ቃለ መጠይቅህ ዋና ይዘት አድማጮችህን አስታውሳቸው ፡፡ ባለሙያው ከሠጣቸው ማብራሪያዎች መካከል የተወሰኑትን ግለፅላቸው፡፡ ለምሳሌ :- እንዲህ ማለት ትችላለህ፡
      • "ፓሸንስ አብዱላይ ከ ቱሙ በአፈር ጥበቃ ስራ ላይ የሰጠችንን ተሞክሮዋን ነበር ስታደምጡ የቆያችሁት ፡፡ አሷ ያገኘቻቸው ሶስት ትልልቅ ጥቅሞችን ስትገልፅ ነፍሰጡር በመሆኗ እረፍት ስለሚያስፈልጋት ቁጡብ እርሻ "minimum tillage" ለእርሷ የቀለለ ሆኖላታል፡፡ ሰብል እየቀያየሩ ማምረትም ቤተሰብዋን የአዝርዕቶቻቸውን ዓይነቶች የተለያዩ እንዲሆኑ ረድቷቸዋል፡፡ይህም በምግባዊ ይዘቱም ለገበያ አማራጭም ጠቅሟቸዋል፡፡ በመጨረሻም ለተወሰኑ ዓመታት የአፈር ጥበቃ ስራን በመስራትዋ ጤናማ አፈር ማለት የተሻለ ምርት ማለት መሆኑን መረዳት እንደጀመረች እንዲሁም ምንም እንኳን ጥቂት ዓመታት ቢወስድም አሁን አሁን ለውጥ እያመጣ እንደሆነ ገልፃለች፡፡ እንዲህ አትበል ፡- "ፓሸንስ አብዱላይ ከ ቱሙ የአፈር ጥበቃ ጥቅሞችን ስትነግረን ነበር የሰማቹኋት"
    • የሸፈንካቸውን ዋና ዋና ነጥቦችን ቃለ መጠይቅ ሰጪው እንዲያጠቃልልልህ መጠየቅ ትችላለህ፡፡
    • አድናቆትህን ግለጽ/Express appreciation/: ለምሳሌ፡-
    • "ዛሬ እዚሁ ከእኛ ጋር በመሆን ሃሳብህን ስላካፈልከን እጅግ እናደንቅሃለን በቀጣይም በፕሮግራሙ እንምትገኝልን ተስፋ እናደርጋለን፡፡" ወይም በቀላሉ : "ዛሬ ከፕሮግራመችን ጋር ስለነበርክ እናመሰግናለን"
    • በትክክል መቅረፅህን፤ ማንን እንዳናገርክ ከሚነግርህ ስም ጋር በትክክል ፅፈህ ማስቀመጥህን፤ ከነቀኑ እና ርዕሱ መያዝህን አረጋግጥ፡፡

    3. አክብሮት ይኑርህ

    ለቃለ መጠይቅ አድራጊው እና ለባለሙያው :

    • ቃለ መጠቅህን በመጨረሻው ሰዓት መሰረዝን አስወግድ ፡፡ ሌላው ሰው ግዴታዎች እንዳሉበት አክብር ፤ ቃለ መጠይቁን መሰረዝ ካለብህም በተቻለ መጠን እስታውሰው፡፡
    • ማቆራረጥን በዘላቂነት አስወግድ፡፡
    • ሰዓት አክባሪ ሁን !
    • ሌላውን ሰው በትኩረት አዳምጥ፡፡
    • መሰላቸትን፣ ተስፋ መቁረጥን ፣ እና ቁጣን የሚገልፁ የፊት እና የሰውነት ቋንቋ አስወግድ፡፡
    • ባትስማማም ራስህን በመነቅነቅ አለመስማማትህ መግለፅን አስወግድ፡፡
    • የሌላውን ልምድ አለመቀበልን አስወግድ፡፡ ለምሳሌ፡- "አይ አርሶ አደሮቹ የዘር አቅርቦትማ አላቸው፡፡ መቀበሉ ላይ ግን በጣም ሰነፎች ናቸው፡፡” ወይም “ባለሙያዎች ለአርሶ አደሮች ፍላጎቶች በፍፁም ትኩረት አይሰጡም፡፡ ስለዚህ ሚንስቴሩም ስለዚህ ጉዳይ ምንም እንደማይሰራ እርግጠኛ ነኝ"
    • እያንዳንዱ ወገን ትክክለኛ እንደሆነ ሲሰማው እና ሌላው ሰው ስህተት መሆኑን ለማስረዳት ወይም በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ዕውቀት እንደሌለው ለማሳየት በሚናገርበት ሁኔታ ላይ ክርክሮችን አስወግድ፡፡

    ለቃለ መጠይቅ አድራጊው :

    • ቃለ መጠይቅህን በመደብክለት ሰዓት አጠናቅቅ፡፡ተጨማሪ መረጃ ለማካተት ከፈለግክ ቃለ መጠይቅ ሰጪውን ጊዜ ካለው ጠይቀው፡፡ ካልሆነ ለሌላ ጊዜ አስፈቅደው፡፡
    • የግል ወይም ተዛማጅ ያልሆኑ ጥያቄዎችን አስወግድ፡፡
    • የቃለ መጠይቅ ሰጪውን ስም አጠራር በተደጋጋሚ መሳሳትን አስወግድ፡፡ እርግጠኛ ካልሆንክ ቃለ መጠይቅ ሰጪውን ቃለ መጠይቅ ከመጀመሩ በፊት በትክክል እንዲጠሩልህ ጠይቅ፡፡
    • ቃለ መጠይቁ መቼ አየር ላይ እንደሚውል አሳውቀው፡፡

    ለባለሙያው :

    • ስልክ ማውራት ፤ ስልክ ላይ መጫወት፤ ወይም መፃፍን አስወግድ፡፡ ስልክህን ወይ ማጥፋት ወይ ድምፁን ማውረድ ይኖርብሃል፡፡
    • ቃለ መጠይቁን በተቻለ መጠን ለማሳጠር በሚል ስሜት እስኪታወቅብህ ድረስ በጣም አጭር መልስ መስጠትን አስወግድ፡፡
    • የመቅረፀ ድምፅ መሳሪያዎችን መያዝ የ ፕሮንራሙ አዘጋጅ ሃላፊነት መሆኑን አስታውስ፡፡
    • አዘጋጁን ዕውቀት እንደሌለው ዓይነት አድርገህ በንቀት ማየትን አስወግድ፡፡
    • ጊዜውን አንተ አትቆጣጠረው ፡፡ ቃለ መጠይቅ ጭውውት እንጂ የአንድ ወገን መግለጫ ኣይደለም፡፡
    • በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ ብቻ መልስ፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ስላላነሳው ጥያቄ መረጃ መስጠት ከጀመርክ ቃለ መጠይቁን በሙሉ ልትስተው ትችላለህ፡፡
    • አዘጋጁ ለአድማጮቹ መረጃን በመስጠት እያበረከተ ያለውን ሚና አድንቅለት ፤ እንዲሁም መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም የግብርና ዕውቀትህን በማካፈል ላይ ያለህን ፍላጎት አሳይ፡፡
    • የመከታተያ/ምርመራ ጥያቄዎችን ማቅረብ የአዘጋጁ የስራ አካል መሆኑን አስተውል፡፡ አዘጋጁን ከማደናቀፍ (ተስፋ ከማስቆረጥ) ይልቅ በቅንነት ተቀበለው፡፡
    • የበላይነት ስሜትን አስወግድ፡፡
    • የቃለ መጠይቁን ይዘት የመቀየር ሃሳብህን እና ጥቅም ላይ የማይውል ማቴሪያል መጠየቅን አስወግድ፡፡
    • በተከታታይ ስለ ሙያ መስክህ ለአዘጋጁ ማስታወስህን አስወግድ፡፡
    • በተደጋጋሚ የቃለ መጠይቅ አድራጊው ጥያቄዎች ቀጥታ በመመለስ ፈንታ ጥያቄዎቹን ደግመህ ማብራራትን አስወግድ፡፡ ለምሳሌ ፡-ቃለ መጠየቅ አድራጊው "ምን ዓይነት አረሞች ናቸው በቆሎን የሚጎዱት?" ብሎ ቢጠየቅህ ጥያቄውን እንደሚከተለው አታብራራው ለምሳሌ፡- "ስለዚህ ከቦቆሎ ጋር ስለሚካፈሉ አላስፈላጊ አረሞች ካወራን ቅድመ አደጋ እና ድህረ አደጋ ፤ ምን ነበሩ ሁለቱም ዝርያዎች ?"

    4. ጥሩ የቃለ መጠይቅ ቴክኒኮችን ተጠቀም

    ለቃለ መጠይቅ አድራጊው እና ለባለሙያው፡-

    • ጥያቄ እና መልሶቹ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ እያጠነጠኑ መሆናቸውን አረጋግጥ፡፡
    • የሬድዮ ቃለ መጠይቅን የአንድ ለአንድ ጭውውት እንደሆነ አድርገህ አስብ፡፡አክባሪ እና ጓደኛዊ ሥሜት ይኑርህ፡፡ሆኖም ግን እንደ ጓደኛ ከምታወራው ይልቅ በመጠኑ ንግግርህ መደበኛ ይሁን ፡፡
    • የቃለ መጠይቅ ርዝመት : በተወሰነ መልኩ የቃለ መጠየቅ ትክክለኛ ርዝመት በቃለ መጠይቁ ዓላማ እና በፕሮግራሙ ዓይነት ለይ የተመሰረተ ነው፡፡ በመጋዚን ፕሮግራም የታረመው ቃለ መጠይቅ ከሌሎቹ የፕሮግራሙ ይዘቶች ጋር መስማማት ይኖርበታል፡፡ ልብ በል በአንድ ርዕስ ከግብርና ተማራማሪ ጋር ወይም ከግብርና ኤክስቴንሽን ሰራተኛ ጋር የ 15 ደቂቃ ቃለ መጠይቅ በአንዴ አዳምጦ ለመረዳት በጣም የበዛ መረጃ ሊሆንበት እንደሚችል አስብ፡፡ በምትኩ ከ3-5 ደቂቃ መረጃ ብትጠቀም በቂ ነው፡፡ የተለያዩ አገራት የቃለ መጠይቅ ርዝማኔ ምን ያህል ሊሆን ይገባል በሚለው ጉዳይ ሊለያዩ ይችላሉ ነገር ግን ዋናው ዓላማው አርሶ አደሮች ሊያስታውሱት የሚችሉት ጠቃሚ መረጃ መስጠት መሆኑን አትርሳ፡፡ ከቃለ መጠይቁ በፊት ቃለ መጠይቅ ሰጪውን ለቃለ መጠይቁ የተያዘው ጊዜ 5 ደቂቃ መሆኑን አሳውቀው ፤ከዚያም ብዙ ሳትቆራርጥ ለመስራት ሞክር፡፡
    • ለተሻለ ሬድዮ ባለሙያዎች በአንድ ጊዜ ከአዘጋጁ ጥያቄ ወይም ኢድምፃዊ መልዕክት ውጭ ከጥቂት ደቂቃ በላይ ማውራት የለባቸውም፡፡ ለማብራሪያ ሲል ፤ ሌላ እይታ እንዲጨመር ሲፈልግ ፤ እንዲሁም ቃለ መጠይቅ አድራጊው እና አድማጮች እየተግባቡ መሆናቸውን ለማረጋግጥ ሲፈልግ ቃለ መጠይቁን የመቋረጥና በመሃል የመጠየቅ መብት ያለው የአዘጋጁ (የቃለ መጠይቅ አድራጊው ) ነው፡፡

    ለቃለ መጠይቅ አድራጊው :

    • ባለሙያው ጉዳዮችን በግልፅ ቋንቋ እንዲገልፅልህ ጠይቀው፡፡ የጋራ ያልሆኑ(ያልተለመዱ) ቃላትን አለመጠቀም፡፡ ያልተለመዱ ስንል ቴክኒካዊ ቃላት አይደሉም፡፡ በቀን ተቀን የአድማጮች ቋንቋ ጥቅም ላይ የማይውል ማንኛውም ቃል ያልተለመደ "jargon" ነው፡፡ ለምሳሌ አዘጋጆች የአከባቢውን ቋንቋ መጠቀም የሚችሉ ቢሆንና ነገር ግን ግብርና ነክ፣ የጤና አባባሎችን በእንግሊዝኛ ፣ ወይም በፈረንሳይኛ ቢቀላቅሉ ይህ ለተመልካቾች ያልተለመደ “ jargon” ነው፡፡ ለማንኛውም በአከባቢው ቋንቋ የተሻለ ቃላትን ፈልግ፡፡
    • ባለሙያዎች ነገሮችን እንዲገልፁልህ በቂ ጊዜ ስጣቸው፡፡
    • አስፈላጊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ የአማራጭ ዘዴዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ ባለሙያዎች ወደ አንደኛው አቋም እንዲወስዱ አትገፋፋቸው፡፡

    ለባለሙያው፡-

    • ለአድማጮችህ ሊገባቸው በሚችል ቋንቋ አውራ፡፡ ለምሳሌ ፡- እንደሚቀጥለው አትበል "የህይወታዊነት ዳታ(ባዮ ዳታ) መረጃ 100% ሞትን ያሳያል," እንዲህ ከማለት ይልቅ እንደሚከተለው በለው “ዓሳዎቾ በሙሉ መተዋል፡፡” ሊወገዱ የማይችሉ ነገር ግን ጠቃሚ የሆኑ አባባሎች (ቴክኒካዊ ሊሆኑ ጭችላሉ) በሚገባ ቋንቋ አብራራቸው፡፡
    • ኣላስፈላጊ እና የተንዛዙ መልሶች መስጠትን አስወግድ፡፡ መልሶችህን ከተሰጠህ ሠዓት ጋር አጣጥማቸው፡፡
    • አንድን ዓይነት እይታ ከሚገባ በላይ አትደጋግም፤ ለአድማጭ ጠቃሚ መረጃ ለመስጠት አየር ላይ መሆንክን አስታውስ፡፡

    5. የሳይንስ ባለሙያዎችን እና የአርሶ አደር ባለሙያን ቃለ መጠይቅ ማድረግ ልዩነት አለው?

    • የሳይንስ ባለሙያዎች ስኬታማ እና መረጃ ሰጪ ቃለ መጠይቅ የሚሰጡ ፤ ሁሉን ነገር የሚያውቁ ተደርጎ የሚታሰብበት ኋላ ቀር ግንዛቤ አለ፡፡ እውነታው ግን ቃለ መጠይቅ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ የሆኑ የሳይንስ ባለሙያዎች እንዳሉ ሁሉ ውጤታማ ያልሆኑ የሳይንስ ባለሙያዎችም አሉ፡፡ ውጤታማ ያልሆኑትም ሆኑ ውጤታማ የተባሉት ቃለ መጠይቅ ሰጪዎች ለአድማጭ ጠቃሚ የሆነ ቃለመጠይቅ ለማካሄድ የቃለ መጠይቅ አድራጊው መሪነት ያስፈላጋቸዋል፡፡ ለምሳሌ ፡- የሳይንስ ባለሙያዎች ቃለ መጠይቅ ሲሰጡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ቃለመጠይቁን እንደሚመራው ሊረዱ ይችላሉ እናም ራሳቸው እንዲመሩት ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ አዘጋጁ ቃለ መጠይቁን እንዲያቋርጡ ሲደረጉ ምቾት ላይሰማቸው ይችላል፡፡ ከቃለ መጠይቁ በፊት በተለይ የቃለ መጠይቅ ልምድ የሌላቸው ሲሆኑ በቃለ መጠይቁ ወቅት ምን እንደሚጠበቁ አሳውቀቸው፡፡
    • በአጠቃላይ የሳይንስ ባለሙያዎች እይታ በጥናት በተገኘ ዕውቀት የሚያጋድል ሲሆን ፤ የአርሶ አደሮች እይታ ደግሞ ከቀን ተቀን በሚገኝ ልምድ እና ተሞክሮ እምዲሁም ከባህላዊ ዕውቀት የሚመነጭ ነው፡፡
    • ከአርሶ አደር ባለሙያዎች የሚደረጉ ቃለ መጠይቆች በተለየ ሁኔታ በችግሮች ፤ በትግል ፤ እና በስኬት ታሪኮች ላይ የሚያጠነጥኑ ሲሆን ከባለሙያዎች ጋር ሲሆን ግን በአብዛኛው ቴክኒካዊ መረጃ ላይ ያተኩራሉ፡፡.
      • "ቁልፍ ልዩነቱ የእይታ ጉዳይ ነው፡፡ የአርሶ አደሩ እይታ የግል ተሞክሮን መሰረት ያደረገ ሲሆን የባለሙያው እይታ ግን የፅንስ ሀሳብን እና ምልከታን ያጣመረ ሊሆን ይችላል"
    • የሳይንስ ባለሙያ ጥናቶችን እየጠቀሰ አጠቃላይ እና ስምምነት የተደረሰባቸው በባለ ሙያው ማህበረሰብ የተረጋገጡ መረጃዎችን ይሰጣሉ፡፡መረጃዎቹ አስተማማኝ እንዲሆኑ ይጠበቃል፡፡ አርሶ አደር ባለሙያ የአከባቢውን የግል ተሞክሮን መሰረት ያደረገ ዕውቀት መረጃውን ይሰጣል፡፡ ይህ መረጃ በተወሰነ ደረጃ ከግል ስሜት ጋር የተያያዘ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡

    6. የፍላጎት መጋጨት፤ በዕውቀት ላይ የተለያዩ እይታዎች

    ከባለሙያዎች ጋር ቃለመጠይቅ ስታደርግ ግለሰብ ባለሙያዎች አርሶ አደሩ አድማጭ ከሚፈልገው ውጪ የተለየ ፍላጎት ሊኖራቸው እንደሚችልም አስብ፡፡ ለምሳሌ ፡-አንድ ባለሙያ ለአንድ የዘር ሽያጭ ድርጅት የሚሰራ ይሆንና፤ በቃለመጠይቁ ወቅት ድርጅቱን ማስተዋወቅ ሊፈልግ ይችላል፡፡ በእንደነዚህ አጋጣሚዎች ቃለ መጠይቅ አድራጊው ፤ ባለሙያው ለአንድ የአከባቢው አርሶ አደሮችን አንድ የዘር ዓይነት እንዲጠቀሙ ለማሳመን እየሞከረ ለሚገኝ የዘር ሽያጭ ድርጅት እንደሚሰራ አስተዋውቀው፡፡

    ባለሙያዎችም- የኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ፤ ተማራማሪዎች፤ ወይም አርሶ አደሮች ከፍተኛ ዕውቀት ሊኖራቸው ይችላል ፤ ሆኖም ግን አይሳሳቱም ማለት አይደለም፡፡ ሁሌም ፍፁም አይሆኑም፡፡ በአንዳንድ ርዕሰ ጉዳዮች አንድ ብቻ ትክክል የሚባል መልስ ላይኖረው ይችላል፡፡ተማራማሪዎች እና የኤክስቴንሽን ሰራተኞች በቅንነት ላይስማሙ ይችላሉ፡፡ ለአድማጭ አርሶ አደሮች የሚስማሙ ሁሉም አስፈላጊ አማራጮችን ማጉላት የቃለመጠይቅ አድራጊው ስራ ነው፡፡ ቃለመጠይቅ አድራጊዎች የቻሉትን ያህል እጅግ ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ለማስተላለፍ ራሳቸውን በአድማጮቻቸው ቦታ ያስቀምጣሉ፡፡ ይህ ከባድ ጥያቄዎች መጠየቅን ሊያካትት ይችላል፡፡ ምክንያቱም በጣም ጠቃሚ የሆነው ጥያቄ ባለሙያው ከተናገረው ወይም ለማስተላለፍ እየሞከረ ካለው መልዕክት የተለየ ሊሆን ይችላል፡፡ (ይህን አድራሻ የመልከቱ ፤ F.A.I.R. journalism standards for farmer programs

    7. ችግርን መፍታት

    ቃለ መጠይቅ ሰጪው ባለሙያ ዙሪያ ጥምጥም ወይም የማይጨበጥ መልስ መስጠቱን ቢቀጥል ቃለ መጠይቅ አድራጊው ማድረግ ያለበት ምንድነው ?

    • ጥያቄህን አብራራ
    • መቅረፀ ድማፅህን በማስቆም ባለሙያውን ቀጥታዊ መልስ መስጠት ላይ ትኩረት እንዲያደርግ አበረታታው ፡፡ የሚሰጣቸው መልሶች አድማጮች በግልፅ ሊረዱት እንደሚገባ አብራራለት፡፡
    • ጥያቄው ማብራራቱን ካልጠቀመ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ከሚከተሉት ዘዴዎች አንዱን በመጠቀም ጥያቄውን ሊያስተዋውቅ ይችላል፡፡ 1) "ይህ ጉዳይ በጣም ጥሩ ነው ሆኖም ግን ለአድማጮቻችን ይበልጥ ቢያውቁት አስፈላጊ የሚመስለኝ …" ወይም 2) "ይቅርታ ይህ ነገር ግልፅ እንዲሆንልኝ እፈልጋለሁ………….."
    • ቃለመጠይቁ የቀጥታ ስርጭት ላይ ከሆነ አድማጮች ቅር እንዳይላቸው ቶሎ አቋርጠው፡፡ እየተቀረፀ ከሆነ ግን የመረጃ ክፍተት እናዳይፈጠርብህ ሌላ ባለሙያ እንደምትጠይቅ እርግጠኛ ሁን፡፡

    ቃለ መጠይቅ የሚሰጠው ባለሙያ ከሚሰጠው ምላሽ የአንዱን ትክክለኛነት ቃለ መጠይቅ አድራጊው ቢጠራጠረው ምን ማድረግ ይኖርበታል ?

    • በተጨማሪ ጥያቄዎች ጠለቅ ያለ መልስ እንዲሰጥበት አድርግ ፤ የመረጃውን ትክክለኛነት የሚያጠናክር ማስረጃ መጠየቅም ትችላለህ፡፡
    • መልሱ እውነታ ወይም የግል አስተያየት መሆኑን ቃለመጠይቅ ሰጪውን ጠይቅ፤ ቀጥሎም ከነፃ ምንጭ ለማረጋገጥ ሞክር፡፡
    • ባለሙያው እስኪጨርስ ጠብቅ ፡፤ በመቀጠል ከሌላ ምንጭ የሰማኸውን የተለየ መረጃ በትህትና በማቅረብ ባለሙያው ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥህ ጠይቅ፡፡
    • ባለሙያውን እንዲህ በማለት በትህትና ጠይቅ "በዚህ ጉዳይ በ ……………………የተሰጠውን አስተያየት እንዴት ታየዋለህ ?"

    በቃለ መጠይቅ ወቅት ቃለ መጠይቅ አድራጊው በግብርና ጉዳይ ላይ የተሳሳተ መረጃ ሲሰጥ ባለሙያ ቢሰማ ምን ማድረግ አለበት?

    • በቀላሉ ትህትና በተላበሰ ሁኔታ ማስተካከያ አድርግ ፤ ማን ማንን በለጠ ሳይሆን ስራው የቡድን መሆኑን አስታውስ፡፡
    • ቃለ መጠይቁ እየተቀረፀ ከሆነ ባለሙያው ሁኔታውን በማብራራት ቃለ መጠይቅ አድራጊውን ማረም አለበት፡፡

    በቃለ መጠይቅ ወቅት ቃለ መጠይቅ አድራጊው ባለሙያው ሙሉ መልስ ለመስጠት መብቱ በሌለው ጉዳይ ላይ እንዲመልስ ቢጠይቀው ባለሙያው ምን ማድረግ አለበት ?

    • ባለሙያው በተቻለ መጠን ብዙ መልስ መስጠት አለበት፡፡ ሆኖም ይበልጥ አስፍቶ ለመመለስ ግን መብቱ ወይም ነፃነቱ እንደሌለው ግለፅ፡፡ እንዲሁም ለምን ለሚል ጥያቄ በተቻለ መጠን አብራራ፡፡ ባለሙያው በተጨማሪም ቃለ መጠይቁን ሙሉ በሙሉ ሊመልስ ወደሚችል አካል ሊያዛውረው ይችላል፡፡
    • ባለሙያዎች በራሳቸው ጊዜ መልስ እንዲሰጡባቸው በማይፈቀዱላቸው ርዕሶች ላይ መልስ ከመስጠት መቆጠብ አለባቸው፡፡ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ መስጠት ይችላሉ፡፡ እንደ ርእሰ ጉዳዩ ይዘት ድምፃቸው ሳይቀረፅ እና ማንነታቸው ሳይፃፍ መረጃውን መስጠት ይችላሉ፡፡

    8. ጥሩ ቃለ መጠይቅ እንዳይኖር የሚያደርጉ ባህላዊ ልማዶች እና ሌሎች ዕንቅፋቶች

    በቃለ መጠይቅ ወቅት ባህሎችና ልማዶችን ጨምሮ በቃለ መጠይቅ ወቅት ሙሉ መግባባት እንዳይኖር እንቅፋቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ባህሎችና ልማዶችን የማወቅ ፈንታ እንዲሁም እነሱን አክብሮ የሚፈልገውን መረጃ ለማግኘት ጥረት ማድረጉ የቃለ መጠይቅ አድራጊው ነው፡፡

    9. ወንዶች ሴቶችን ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉ እና ሴቶች ወንዶችን ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉ

    (በዚህ አድራሻ ይመልከቱ ሴት አርሶአደሮችን እንዴት በሚገባ ማገልገል ትችላላችሁ)

    ሴት አዘጋጅ እና ወንድ ባለሙያ :

    • ቃለ መጠይቅ አድራጊዋ በትክክል እና አክብሮትን የሚያሳይ አለባበስ ሊኖራት ይገባል፡፡
    • ለሁለቱም ለቃለመጠይቁ ምቾት እንዲሰማቸው እና በነፃነት እንዲናገሩ የሚያደርጋቸው ለቃለ መጠይቅ የሚሆን ቦታ ይምረጡ ፡፡ ለሴቷ ካስፈለጋት ቃለ መጠይቋን አቋርጣ ለመሄድ ብትፈልግ ግልፅ መንገድ ያለው ይሁን፡፤ ለምሳሌ ቃለመጠይቅ ሰጪው ሊተናኮላት እንደሚችል ከሁኔታው ከገመተች፡፡
    • ስም እና አድራሻን በትክክል መጠየቅሽን እና መጠቀምሽንን አረጋግጪ ፡፡ ለምሳሌ ፡ ደክተር ፣ፕሮፌሰር ፣ ወይዘሪት፣ ወዘተ በሚል ሰዎችን በትክክል ጥሪ፡፡ ባለሙያ መሆናቸውን መጨመር አያስፈልግም፡፡ በቀላሉ ስም እና ማዕረጋቸውን ብቻ መጠቀም ትችያለሽ፡፡ ካስፈለገም የስራ ድርሻቸው እና መተዳሪያዎቻቸውን መግለፅ ትችያለሽ፡፡ በዚህ ዘዴ እነዚህን ሰዎች ባለሙያ መሆናቸውን በአንፃሩ አርሶ አደሮች ሙያ እንደሌላቸው የሚያንፀባርቅ ስሜትን አስወግጂ፡፡
    • ፆታ ነክ አባባልን አስወግጂ፡፡ ለምሳሌ ፡- ባለሙያው ሴት ቃለ መጠይቅ አድራጊ የግብርና ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንደሌላት የሚገልፁ ከኣከባቢ እና ቤተሰብ ህይወት ብቻ የተወሰዱ ምሳሌዎችን ሊሰጥ ይችላል፡፡
    • ሙያዊ ሁኚ ትክክለኛ ያልሆኑ የሰውነት እና የምልክት ቋንቋዎችን አጠቀቃም ላይ ጠንቃቃ ሁኚ፡፡

    ወንድ አዘጋጅ እና ሴት ባለሙያ:

    • ፆታ ነክ አባባልን አስወግድ ፡፡
    • ሙያዊ ሁን ትክክለኛ ያልሆኑ የሰውነት እና የምልክት ቋንቋዎችን አጠቀቃም ላይ ጠንቃቃ ሁን፡፡
    • ከባለሙያው በኩል ሊኖር የሚችል በባህል ዘንድ ተቀባይነት ያለው ልዩነትን አክብር፡፡
    • ቃለ መጠይቁን ቀን ላይ ለማካሄድ በእርግጠኛነት ወስን ፡፡
    • ትክክለኛእና አክብሮት ያለው አለባበስ ተጠቀም፡፡
    • ሴቶችን ከወንዶች ጋር ባላቸው ግንኙነት ተጠቅመህ ማስተዋወቅን አስወግድ፡፡ (ለምሳሌ፡- እናት፣ ሚስት፣ ወዘተ) እንዲሁም አካላዊ ሁኔታቸውን ጠጠቅመህ ማስተዋወቅን አስወግድ (ለምሳሌ፡- "ማራኪ"). በምትኩ ወንዶችን በምታስተዋውቅበት ዘዴ በቀላሉ ትክክለኛ ስማቸውን እና የስራ ድርሻቸውን መጠቀም ትችላለህ፡፡
    • የባለሙያዋን ሙያዊ ሁኔታ አረጋግጠህ ለዎንዶች የሰጠሃቸውን ያህል ተገቢ አክብሮት ስጥ፡፡

    10. ግንኙነቱን ገንባው፡፡

    • ጊዜን በማክበር የተገነባውን አመኔታ (ለሁለቱም ወገን) አዘጋጁም ቃለ መጠይቅ ሰጪውን ቃለ መጠይቁ መቼ እንደሚተላለፍ በማሳወቅ ግንኙነቱን ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
    • ቃለ መጠይቅ አድራጊዎች ባለሙያውን ፕሮግራሙ በሚተላለፍበት ጊዜ እንዲከታተል በማስታወስ ግብረመልስ እንዲሰጥ ፤ እና በሚከሰቱ ጉዳዮች ስለሚታገሉበት አቅጣጫ ለመወያየት ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይገባል፡፡
    • መደበኛ ግነኙነትን መጠበቅ ትስስርን ለማስቀጠል እና ባለሙያው ለቃለ መጠይቅ ሲሆን ብቻ እንደሚፈለግ የሚመስል ስሜትን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ አብነታዊ ታሪኮችን ስታስተላልፍ ባለሙያዎችን አካትት፡፡
    • መደበኛ ተባባሪዎች በተወሰኑ መንገዶች የቡድኑ አካላት ይሆናሉ፤ እናም ሊዘጋጁ በሚገባቸው ፕሮግራሞች ርዕሶች ዙሪያ ለመወያየት መሰብሰብ ይቻላል፡፡
    • ቃለ መጠይቅ አድራጊው ባለሙያዎቹን በድጋሚ በሌላ ቃለ መጠይቅ ሊያገኛቸው እንደሚችል ሊገልፅላቸው ይገባል፡፡ ስለዚህ ጠለቅ ያለ መገናኘ ዘዴ መያዝ (መቀበል) ያስፈልጋል፡፡
    • ትራንስፖርት እና የአየር ሰዓት ወጪን የሚሸፍን ትክክለኛ ማካካሻ መስጠት ትክክል ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ግን ይህ በፕሮግራሙ በመሳተፋቸው የሚሰጥ ዓይነት ክፍያ ተደርጎ በፍፁም ሊታይ አይገባም፡፡
    • ለመደበኛ ተባባሪዎች ዓመታዊ የግምገማ እና የዕቅድ ስብሰባ ለማዘጋጅት አስብ፡፡
    • ከመደበኛ ተባባሪዎች ጋር ማብራሪያ የምትጠይቅበትን እና ግብረመልስ የምታሰባስብበትን ለክትትል እና የፓነል ውይይት የምታዘጋጅበትን ጊዜ ፍጠር፡፡

    ከባለሙያዎች ጋር ስለሚደረግ ቃለ መጠይቅ በተጨማሪ ከየት መማር እችላለሁ ?

    ኔክታሪ፤ቀኑ ያልተጠቀሰ “The Do’s & Don’ts Of Subject Matter Expert Interviews.” http://nectafy.com/subject-matter-expert-interviews/

    ምስጋና

    አስተዋፅኦ ያደረጉ : ቪጄ ኩድፎርድ በፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ማኔጂንግ ኤዲተር እና በፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ሲልቪ ሃሪሰን የሬድዮ ሙያ ዝግጅት ቡድን መሪ፡፤ የፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል የዳይረክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ዱዋግ ዋርድ ፣እና በፋርም ሬድዮ ኢንተርናሽናል ሲንየር አማካሪ ዴቪድ ሞውብሬ

    የዚህ ሰነድ ዝግጅት በካናዳ ዓለምአቀፍ የልማት ጥናት ማዕከል (IDRC) በካናዳውያን ዓለም አቀፍ የምግብ ዋስትና ጥናት ፈንድ በኩል (CIFSRF).
    የተደገፈ ነው፡፡

    ህ ፕሮጀክት የካናዳ መንግስት ፋይናንስ በካናዳ ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች በኩለ በሚሰጠው ድጋፍ የሚሳለጥ ነው፡፡
    ይህ ሰነድ ወደ አማርኛ የተተረጎመው በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለስቴፕልስ ፕሮጀክት በሰጠው ድጋፍ ነው፡፡

    ይህ ሰነድ ወደ አማርኛ የተተረጎመው በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለስቴፕልስ ፕሮጀክት በሰጠው ድጋፍ ነው፡፡

    የመረጃ ምንጭ
    የሚከተሉት ሰዎች ለዚህ የአዘጋጆች መመሪያ ኣብዛኛው ክፍል ግብአት በማመንጨት እና ተከታይ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ተባብረዋል፡፡
    አዘጋጆች:

    ሸይላ ቺምፋምባ፤ ዞዲካ የማሰራጫ ጣቢያ ማላዊ
    ጃምስ ጉምባዋ፤ ማላዊ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፤
    ኢዛክ ቢ ምዋቻ ሬድዮ ማሪያ፣ ታንዛኒያ
    ሞሃመድ ኢሳ አቡድ ሚድያ ፤ ታንዛኒያ
    ጆን ምካፓኒ ንክሆታኮታ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ፤ ማላዊ
    ጊድየን ክዋሜ ሳርኮዲዮሰይ፤ ADARS FM, ጋና
    ኮለታማኩልዋ፤ ሳሃራሚድያ፤ ታንዛኒያ
    ዶንጎ ሳራ ፤, ሜጋ ኤፍ ኤም ዩጋንዳ
    ሙቢሩ አሊ፤ሬዲዮ ሲምበ ዩጋንዳ
    ኦማሩሲዲቤ ፤ RTB2/Bobo, ቡርኪናፋሶ
    ኮሎማይሬኔ ሳዮን፤ ሬድዮ ካፎ ካን-ማሊ
    ሳሙኤል ቲ ሳዋዶጎ፤ ሬድዮ ማነግዳ ቡርኪናፋሶ

    ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ፤ ተማራማሪዎች እና ሌሎች :
    ሳኡሎሲካቺትሳ፤ ትራንስፖርት እና የፐብሊክ ስራዎች ሚኒስቴር ፤ ማላዊ
    አስናርትኒረንዳ፡ የግብርና ምርምር አገልግሎቶች ፡ማላዊ
    ፉላ ያሲን ፡ ሎንጊዶ ዲስትሪክት ካውንስል ታንዛንያ
    ዳንለይ ኮሌክራፍትአይዱ ፡ ጋና -ሌጎን ዩኒቨርሲቲ
    ፓስቻል አቴንግደም የጋና – አክራ ዩኒቨርሲቲ
    ስቴላ አበር ፤ ወርልድ ቪዥን ዩጋንዳ
    ፊሊፕ ቺዳዋቲ ማላዊ ወተት አምራቾች ማህበር
    ጆን ምሴሞ፤ የግብርና ሚኒስቴር የከብት እርባታ እና አሳ አጥማጆች ፤ ታንዛን
    ቱምዌሲጅ ጁሌስ፤ ፍሪካ 2000 ኔትወርክ ዩጋንዳ
    ደሪስ ዳርተይ፤ ብሔራዊ ሚድያ ኮሚሽን ጋና
    ሪቻርድ ባምባራ፤ ONG LVIA, ቡርኪ ናፋሶ
    ሞሳ ኮኔ፤ የእንስሳት ተዋፅኦ አከባቢያዊ ግልጋሎት (SLPIA), ቦጎኒ ፤ ማሊ